የኢመየብማ ኮአክሽን መዋዕለ ሕፃናት
የኢመየብማ ኮአከአሽን መዋዕለ ሕፃናት ዓለም አቀፍ የሕፃናት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ከተከበረ በኋላ የተቋቋመ ነው። በወቅቱ በማዘር ቴሬዛ የሚካሄድ የበጎ አድራጎት እህቶች የሚባል ማኅበሩ ካለበት አካባቢ አቅራቢያ ይገኝ ነበር። ከነዚያ እህቶች መካከል ሁለቱ በድርጅታቸው እንክብካቤ ሥር የነበሩ ሁለት መስማት የተሳናቸው ሕፃናት (አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት) ይዘው በመምጣት ማኅበሩ እንዲያስተምርላቸው ጠየቁ። ማኅበሩም ጥያቄያቸውን ላለመቀበል እና አላስተምርም ለማለት የማይቻለው ሆኖ አገኘው። በመሆኑም ሕፃናቱን በሳምንቱ የሥራ ቀናት ውስጥ በየቀኑ ለግማሽ ቀን ለማስተማር ተስማማ። ይህ የሆነው በ1974 ዓ.ም. ነበር።
የተጨማሪ ሕፃናት መምጣት
ሌሎች ወላጆችና የማኅበሩ ወዳጆች ማኅበሩ ሕፃናት ማስተማር መጀመሩን እንዳዩ ሌሎች ሕፃናትም ማምጣት ጀመሩ። በዚህ መንገድ የማኅበሩ መዋዕለ ሕፃናት ሊጀመር ቻለ። ይህ በሆነበት ወቅት ዓለም አቀፍ የሕፃናት ዓመት በ1971 ዓ.ም. ተከብሮ በ1973 ደግሞ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ዓመት በተባበሩት መንግሥታት ታውጆ እየታሰበ ነበር። ማኅበሩም ይህንን አስታኮ ለመስማት የተሳናቸው የሚሆን የሕፃናት መዋያ ለማቋቋም የሚያስችል የፕሮጄክት ሃሳብ አዘጋጅቶ ለዩኔስኮ የጋራ ተግባር ፕሮግራም ላከ። የማኅበሩ የፕሮጄክት ሃሳብ ተቀባይነት በማግኘቱም በዩኔስኮ የተመረጡ ፕሮጄክቶች በዩኔስኮ ወዳጆች ማኅበራትና ክለቦች ታውቀው እንዲደገፉ ለማድረግ በሚታተሙበት መጽሔት (ብሮሸር) ውስጥ ለመታተም በቃ።
የተመረጡት ፕሮጄክቶች ብሮሸሩ ውስጥ ታትመው ከተሰራጩ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ማኅበሩ እርዳታዎች ይደርሱት ጀመር። እርዳታው ይመጣ የነበረው "ዩኑም ቼክ" ተብሎ ይታወቅ በነበረው ነበር።
ዩኑም ቼክ ዋና ዓላማው ጥቃቅን ግዢዎች ለማካሄድ እንዲቻል ተብሎ የተዘጋጀ ነበር። ኢመየብማ የፈለገው ግን ለሕፃናት መዋያው በቋሚነት የሚያገለግል ቤት ለማሠራት ነበር። በዚያን ወቅት ለማኅበሩ የሚሆን ቦታ ለማግኘት ከመንግሥት ተስፋ ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን በደርግ ጊዜ በነበረው ያልተረጋጋ ሁኔታ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለማኅበሩ ቦታ እንዲሰጥ ተወስኖ የነበረውን ውሳኔ እንዲፈጸም ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። በመጨረሻ ከመንግሥት ለውጥ በኋላ በዩኔስኮ በኩል የተሰበሰበው ገንዘብ ለማኅበሩ የሕፃናት መዋያው አገልግሎት የሚሆን ቤት እንዲገዛበት ተወስኖ ቤት ለመግዛት ተቻለ።
የገንዘብ እርዳታ ምንጭ
በዩኔስኮ በኩል ከዩኔስኮ ወዳጆች ለማኅበሩ ከተሰበሰበው ውስጥ አባዛኛው የተገኘው ከኔዘርላንድስ የዩኔስኮ ማዕከል ነበር። ቀሪው ደግሞ የተገኘው ከጃፓን የዩኔስኮ ማኅበራት ፌደሬሽን ነበር። በፌደሬሽኑ አስተባባሪነት ብዙ ጃፓናውያን ዩኑም ቼክ እየገዙ ለማኅበሩ በፖስታ ቤት በኩል ልከዋል። ከጃፓናውያኑ ሌላ ከአሜሪካ ሁለት ተማሪዎች፣ ከእንግሊዝ ደግሞ አንድ ግለሰብ ዩኑም ቼክ ገዝተው ለማኅበሩ ልከዋል።
ከላይ የሚታየው በዩኔስኮ ፎቶግራፈር የተነሳውን ፎቶ ቀረብ ብሎ በጥልቀት ለተመለከተው ሰው (ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት) ሕፃናቱ የተቀመጡት በፍራፍሬ ሳጥን ላይ መሆናቸውን፣ ጠረጴዛው ደግሞ ዕቃዎችን በመርከብ ለመላክ ከሚያገለግሉ ቁርጭራጭ እንጨቶች የተገጣጠመ መሆኑን ያስተውላል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ይህ ችግር ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ድርጅት (ዩኒሴፍ) በተገኘ አነስተኛ ግን በጣም ጠቃሚ የነበረ እርዳታ ጠረጴዛዎችና የሕፃናት ወንበሮች በማሠራት መፍትሔ ሊገኝለት ተቸሏል። የመጫወቻና ሌሎች የመማርያ ዕቃዎች ደግሞ ከቀድሞው ምሥራቅ ጀርመን መስማት የተሳናቸው እና በከፊል መስማት የተሳነናቸው ፌደሬሽን በእርዳታ ተገኝተዋል።
ቤት ተገዛ
በእርዳታ የተገኘው ገንዘብ ማኅበሩ ለሕፃናት መዋያው ብቻ እንዲያገለግል የታለመ ቤት ለመግዛት ያስቻለው ሲሆን መዋያውም ወደ ቤቱ በ1990 ዓ.ም. ለመግባት ችሏል። እስከዚያው ድረስ የሕፃናት መዋያ አገልግሎቱ ከማኅበሩ ጽሕፈት ቤት በአንድ ጠባብ ክፍክ ውስጥ ሲሰጥ ቆይቶ በዛኒጋባ መልክ ተገንብቶ ወደ ነበረው እና ዝናብ፣ የፀሐይ ሙቀት እና ንፋስ መከለል ወደማይችለው አዳራሽ ተዛውሮ ቆይቶ ነበር።
ቢሆንም አሁን የሕፃናት መዋያው ያለበት ቤትም ቢሆን ብዙ ጉድለቶች አሉበት። ቤቱ በመጀመሪያ ሲገነባ ለመኖርያነት የተገነባ ሲሆን ዲዛይኑም ለመኖርያ ቤትነትም ቢሆን መጥፎ ነው። በመሆኑም ክፍሎቹ ለማስተማሪያነት ብቁ አይደሉም። የቤቱ አንዱ ጥሩው ነጥብ የሚገኝበት አካባቢ ከከተማው መሃል አቅራቢያ እና ተመራጭ በሆነ ቦታ መገኘቱ ነው።
የበጎ አድራጊዎች ጥረት መና ሆኖ አልቀረም
የእርዳታ ሰጪዎች ጥረት መና አለመቅረቱና ውጤት መስጠቱ ማየጥ እጅግ ደስ ያሰኛል። ብዙ መስማት የተሳናቸው ሕፃናት በሕፃናት መዋያው የመጠቀም ዕድል አግኝተዋል። እንዳንዶቹ በአሁኑ ጊዜ የራሳቸው ቤተሰብ አፍርተዋል፤ የአባትነት፣ የእናትነት እና ሌላም ኃላፊነት መሸከም የሚችሉ ብቁ ዜጎች ሆነዋል።
የመዋዕለ ሕፃናቱ ስም
የዩኔስኮ የጋራ ተግባር ፕሮግራም ላደረገው አስተዋጽኦ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የኢመየብማ ሕፃናት ኢመየብማ ኮአክሽን መዋዕለ ሕፃናት ተብሎ እንዲታወቅ ማኅበሩ ወስኗል።
የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ፕሮጄክትን የረዱ ግለሰቦችና ድርጅቶች
ከዚህ ቀጥሎ በሚታየው ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱት ግለሰቦችና ድርጅቶች ለኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ፕሮጄክት እርዳታ ያደረጉ ናቸው። ማኅበሩ መውዕለ ሕፃናቱ የሚገኝበትን ቤት ለመግዛት የቻለው እነሱ ባደረጉት እርዳታ በተገኘ ገንዘብ ነው።
ለኢመየብማ ኮአክሽን መዋዕለ ሕፃናት መቋቋም የረዱ አጋሮች
የዕርዳታ ሰጪ ስም | አገር | ዕርዳታ የተደረጉባቸው ዓመቶች | የዕርዳታ ብዛት |
---|---|---|---|
A friend of NYO | U.S.A. | 1981 | 1 |
Aizu UNESCO Association Youth Club | Japan | 1983 | 1 |
Ms. Akiko Yamazaki | Japan | 1982, 1983 | 4 |
Mr. Akira Satomura | Japan | 1982 | 1 |
Anna Gilmore | U.S.A | 1980 | 1 |
Anonymity | Japan | 1982, 1983 | 4 |
Mr. Atsushi Tani | Japan | 1981 | 1 |
Ms. Chiaki Kato | Japan | 1984 | 1 |
Mr. Eiji Ogino | Japan | 1981 | 1 |
Ms. Eiko Matawari | Japan | 1981 | 1 |
Ms. Eiko Mizuno | Japan | 1983 | 1 |
Dr. F. H. Tunnissen UNESCO CENTRUM NEDERLAND |
The Netherlands | 1979, 1980, 1981, 1982, 1983, 1984, 1985 | 9 |
Fuji Junior High School | Japan | 1981 | 1 |
Ms. Fukiko Yamada | Japan | 1982, 1983, 1984, 1987, 1988 | 6 |
Ms. Fumie Nagabuchi | Japan | 1981 | 1 |
Gyosei-Gakuen Kindergarten | Japan | 1982 | 1 |
Hakodate Club of the Japan Region | Japan | 1982 | 1 |
Hikari UNESCO Youth Club | Japan | 1982 | 1 |
Mr. Hirofumi Mitake/Miyake? | Japan | 1983 | 1 |
Hirosaki Club of the Jaoan Region, | Japan | 1981 | 1 |
Mr. Hisao Otsuki | Japan | 1981 | 1 |
Hirokawa High School UNESCO Club | Japan | 1982 | 1 |
International Year of the Child Memorial Hall | Japan | 1983 | 1 |
Ishikawa-ken UNESCO Association | Japan | 1982 | 1 |
Iwanoda Junior High School, Class No. 1 of the 3rd Grade | Japan | 1982 | 1 |
Mr. J. Roelands | The Netherlands | 1979 | 1 |
Mr. J. Jackson | England | 1980 | 1 |
Karatsu Club of the Japan Region | Japan | 1982 | 1 |
Kawaguchiko UNESCO Association | Japan | 1988 | 1 |
Kawasaki/Kwasaki(?) Club of the Japan Region | Japan | 1981, 1982, 1983 | 3 |
Ms. Kazuko Kitani | Japan | 1981, 1982 | 2 |
Ms. Keiko Takeda | Japan | 1987, 1988 | 2 |
Ms. Keiko Tsuda | Japan | 1988 | 1 |
Kindergarten of Gyosei Gakuen | Japan | 1988 | 1 |
Kinjo-Gakuin University UNESCO Club | Japan | 1985 | 1 |
Kisarazu UNESCO Association Municipal Board of Education | Japan | 1982 | 1 |
Mr. Kiyoshi Tokiwa | Japan | 1983, 1988 | 4 |
Kiyuna St. Andre School | Japan | 1987 | 1 |
Kokusai-Rikai-Bu Morikoka-Kita High School | Japan | 1982 | 1 |
Kokusai-shinzen Club, Dokkyo University | Japan | 1982 | 1 |
Kushiro Club of the Japan Region | Japan | 1982 | 1 |
Ms. Maie Konno | Japan | 1981 | 1 |
Mr. Masao Suzuki | Japan | 1981 | 1 |
Michael & Cyrus Lincoln | U.S.A. | 1981 | 1 |
Ms. Mieko Tanabe | Japan | 1981 | 1 |
Mr. Minoru Murata | Japan | 1981 | 1 |
Nabari UNESCO Association | Japan | 1988 | 1 |
National Federation of UNESCO Associations in Japan | Japan | 1981, 1982, 1988 | 3 |
Nobeoka Club of the Japan Region | Japan | 1982 | 1 |
Ms. Noriko Miyaka | Japan | 1985 | 1 |
Ms. Noriko Miyazaki | Japan | 1984 | 1 |
Okinawa UNESCO Association | Japan | 1988 | 1 |
Okinawa-Ken UNESCO Association | Japan | 1987 | 1 |
Oota UNESCO Association | Japan | 1982 | 1 |
Ota Art Association | Japan | 1981 | 1 |
School of Mission Board in Furuichi | Japan | 1982 | 1 |
Senoue Primary School | Japan | 1984 | 1 |
Shinobu Kato | Japan | 1982 | 1 |
Shiroishi UNESCO Association | Japan | 1985 | 1 |
Suginami UNESCO Association | Japan | 1982, 1987 | 2 |
Takasaki UNESCO Association | Japan | 1981 | 1 |
Ms. Tetsu Kimura | Japan | 1981 | 1 |
Tomioka UNESCO Association | Japan | 1984 | 1 |
Tomioka UNESCO Youth Club | Japan | 1984 | 1 |
Tottori UNESCO Association | Japan | 1988 | 1 |
Tsurugaya Junior High School | Japan | 1987 | 1 |
Mr. Tsuyoshi Obagawa | Japan | 1983, 1985 | 2 |
Ms. Yoshie Mine | Japan | 1985 | 1 |
Mr. Yoshio Saito | Japan | 1985 | 1 |
Mr. Yoshiyuki Hakamada | Japan | 1981, 1983 | 2 |
Mr. Yukio Imaoka | Japan | 1981 | 1 |
Ms. Yumi Tominaga | Japan | 1985 | 1 |