የኢመየብማ መስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ

ባብዛኛዎቹ የበለፀጉት አገሮች ውስጥ አረጋውያን ሲባሉ ዕድማያቸው 65 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናቸው ናቸው። ያ ዕድሜ ባብዛኛው መጦር የሚጀምሩበት የተለመደው ዕድሜ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው ከሆነ "... አንድ ሰው አረጋዊ ሆኗል የሚባልበት አጠቃላይ ስምምነት የተደረገበት የዕደሜ ክልል የለም። ቢሆንም ዕድሜው 60 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነው ሰው አረጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የማሰብ ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት ዘንድ አለ። ኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን ጡሮታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት እንደ መሆኑ መጠን ዕድማያቸው 60 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናቸውን ሰዎች አረጋውያን እንደሆኑ ይታሰባሉ።

መስማት የተሳናቸው አረጋውያን ሴቶች በኢመየብማ የመስማት የተሳናቸው ክለብ ውስጥ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. የእናት ቀን ሲያከብሩ

መስማት የተሳናቸው አረጋውያን ሴቶች በኢመየብማ የመስማት የተሳናቸው ክለብ ውስጥ ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. የእናት ቀን ሲያከብሩ
(ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

ከመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ አባሎች ጥቂቶቹ ከአሜሪካ ከመጡ መስማት የተሳናቸው ጓደኞቻቸው ጋር እማኅበሩ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ኅዳር 3 ቀን 2010 ዓ.ም.

ከመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ አባሎች ጥቂቶቹ ከአሜሪካ ከመጡ መስማት የተሳናቸው ጓደኞቻቸው ጋር እማኅበሩ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ኅዳር 3 ቀን 2010 ዓ.ም.
(ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ አባሎች የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አማኅበሩ አዳራሽ ውስጥ ሲያከብሩ

የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ አባሎች የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን መስከረም 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አማኅበሩ አዳራሽ ውስጥ ሲያከብሩ
(ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር መስከረም 1963 ዓ.ም ሲመሠረት አብዛኞቹ መሥራች አባሎች ወጣቶች ነበሩ። አሁን ማኅበሩ ከተመሠረተበት ጊዜ ከአራት አሰርተ ዓመታት በኋላ ግን እነዚህ መሥራች አባሎች አብዛኞቹ አረጋውያን ሆነዋል። ሆኖም እስከ ታኅሣሥ 2008 ዓ.ም. ድረስ ለማኅበሩ ህልውና ብዙ መስዋዕት ለከፈሉት ለነዚህ አረጋውያን አባሎቹ ማኅበሩ ምንም ያሰበው ወይም ያደረገው ነገር አልነበረም።

ታኀሣሥ 2008 ዓ.ም. ውስጥ ከማኅበሩ አረጋውያን አባሎች ጥቂቶቹ ተሰባስበው የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ መሥርተዋል። ለዚህ ክለብ መቋቋም ግፊትና ቅስቀሳ ያደረጉትም በወቅቱ ማኅበሩን በተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት ይመሩ የነበሩት አባል ሲሆኑ፣ መስማት የተሳናቸው አባሎች አስፈላጊው ትኩረት ከማኅበሩ አለማግኘታቸውን አሳሳቢ ሆኖ ስላገኙት ነበር። በአሁኑ ጊዜ የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለቡ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛል። መስማት የተሳናቸው አረጋውያን እየተገናኙ በጋራ ችግሮቻቸው እርስ በርስ እንዲወያዩ ዕድል የፈጠረላቸው ሲሆን ለማኅበሩም ጥሩ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።

መስማት የተሳናቸው እንግዶችን ተቀብሎ ማስተናገድ

ከኔዘርላንድስ ከመጡት እንግዶች ጥቂቶቹ ከመስማት የተሳናቸው አረጋውያንና ከሌሎች መስማት የተሳናቸው	ጋር የካቲት 5 ቀን 2008 ዓ.ም.

ከኔዘርላንድስ ከመጡት እንግዶች ጥቂቶቹ ከመስማት የተሳናቸው አረጋውያንና ከሌሎች መስማት የተሳናቸው ጋር የካቲት 5 ቀን 2008 ዓ.ም.
(ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

መስማት የተሳናቸው ወጣቶችና አረጋውያን ከኔዘርላንድስ ከመጡት መስማት የተሳናቸው እንግዶች ጋር ኢመየብማ አዳራሽ ውስጥ ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲያከብሩ

መስማት የተሳናቸው ወጣቶችና አረጋውያን ከኔዘርላንድስ ከመጡት መስማት የተሳናቸው እንግዶች ጋር ኢመየብማ አዳራሽ ውስጥ ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲያከብሩ
(ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

እኒህ ከኔዘርላንድስ የመጡ እንግዳ ኅዳር 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ ተገኝተው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ጊዜ የተለማመዱትን የቡና ሥነ-ሥርዓት  እንዳቀረቡ

እኒህ ከኔዘርላንድስ የመጡ እንግዳ ኅዳር 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ ተገኝተው በኢትዮጵያ ቆይታቸው ጊዜ የተለማመዱትን የቡና ሥነ-ሥርዓት እንዳቀረቡ
(ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

መስማት የተሳናቸው አረጋውያን በመደበኛ ሁኔታ እየተገናኙ ከመወያየታቸውም በላይ በተጨማሪም ከውጭ አገራት የመጡ መስማት የተሳናቸው እንግዶች እየተቀበሉ ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፤ ራሳቸውም ተስተናግደዋል። ኔዘርላንድስ ውስጥ Landelijk centrum oudere doven de Gelderhorst (ብሔራዊ የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ማዕከል ?) ከሚባል ለመስማት የተሳናቸው አረጋውያን እንክብካቤ ከሚያደርግ ድርጅት የመጡ የሰሚዎችና የመስማት የተሳናቸው የተካተቱበት ቡድን የካቲት 2008 ዓ.ም. መጥቶ ነበር። ለዚህ ቡድን አባሎች የክለባችን የተወሰኑ አባሎች በየቤቶቻቸው የቡና ሥነ-ሥርዓት መስተንግዶ ያደረጉላቸው ሲሆኑ፣ ቡድኑም ለክለባችን አባሎች የምሳ መስተንግዶ በማድረግ በወቅቱ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ተችሏል። ከዚያ በመቀጠል አራት መስማት የተሳናቸው የተካተቱበት ሌላ ቡድን መጥቶ ለሶስት ወራት የቆየ ሲሆን፣ ከአራቱ መካከል አንዱ አረጋዊ ናቸው። ከዚያ በኋላም ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ መስማት የተሳናቸው የተካተቱበት ቡድን መጥቷል።