የኢመየብማ ቅርንጫፎች

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ኢመየብማ) በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች 28 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አሉት። ማኅበሩ እነዚህን ቅርንጫፎች በማካተት የተለያዩ ፕሮጄክቶች ተግባራዊ አድርጓል።

የ1991 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት አዳማ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የእግር ጉዞ በማድረግ ተከብሯል።

የ1991 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት
አዳማ፣ ኦሮሚያ ውስጥ የእግር ጉዞ በማድረግ ተከብሯል።

(ፎቶ: ከማኅበሩ ስብስብ፤ ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት።)

እያንዳንዱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሚመራው ሰባት የተመረጡ አባላት ባሉት ኮሚቴ ነው። ኮሚቴውም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ባለበት ከተማ ውስጥና በአካባቢው በሚኖሩ መስማት የተሳናቸው አባሎች የተመረጠ ነው። ማኅበሩ ከቅርንጫፍ ኮሚቴዎች ጋር በመተባበር በኤች አይ ቪ / ኤድስ እና ሌሎች የአባለዘር በሽታዎች ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ እና የመከላከል፣ የቤተሰብ ዕቅድ፣ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች እና ሌሎች በሰው አቅም ግንባታ ተግባራት ላይ ሥልጠና መስጠቱን ቀጥሏል።

በጣም ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ መስማት የተሳናቸው የራሳቸው ፈጠራ ከሆኑት ምልክቶች ውጭ መደበኛውን የምልክት ቋንቋ የማወቅ ዕድላቸው በጣም ጠባብ በመሆኑ ከሌሎች ጋር ለመግባባት እንዲችሉ ማኅበሩ መሠረታዊ የምልክት ቋንቋ ሥልጠና ይሰጣል። ይህ ሥልጠና ደግሞ በኤች አይ ቪ / ኤድስ እና በሌሎች ጉዳዮች ያተኮሩ ሥልጠናዎች ለመስጠት በር ይከፍታል።

በእነዚህ ተግባራት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት፣ የክልል እና ንዑሳን ክልላዊ ቢሮዎች አጋርነት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነበር። እንዲያውም አንዳንድ ሥልጠናዎች የተካሄዱት የክልሎች የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች ባቀረቡዋቸው ግብዣዎችና ጥሪዎች ነበሩ።

የኢመየብማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች

ክልልቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
1. አዲስ አበባ አስተዳደር
  1. አዲስ አበባ
2. አፋር ክልል
  2. አሳይታ ከተማ
  3. ሰመራ
3. አማራ ክልል
  4. ባሕርዳር
  5. ደብረብርሃን
  6. ደሴ
  7. ፍኖተ ሰላም
  8. ጎንደር
4. ድሬዳዋ አስተዳደር
  9. ድሬዳዋ
5. የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል
  10. ጋምቤላ ከተማ
6. የሐረሪ ሕዝቦች ክልል
  11. ሐረር
7. ኦሮሚያ ክልል
  12. አዳማ
  13. አምቦ
  14. አሰላ
  15. ባሌ ሮቤ
  16. ጅማ
  17. ነቀምቴ
  18. ሻሸመኔ
8. ሶማሌ ክልል
  19. ጂግጂጋ
9. ሲዳማ
  20. አለታ ዎንዶ
  21. ዲላ
  22. ሐዋሳ
10. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል
  23. አርባ ምንጭ
  24. ሆሣዕና
  25. ዎላይታ ዞን
11. ትግራይ ክልል
  26. ዓዲግራት
  27. አክሱም
  28. መቐለ