ዝርዝር መረጃ (አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ ወዘተ.)

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር (ኢመየብማ)
ፖ.ሳ. 21359
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

ስልክ: +251 11-122-2517 (በገመድ)
+251-118-122610 (አጭር የጽሑፍ መልዕክት መቀበል ይችላል)
+251-942-381712 (ተንቀሳቃሽ ስልክ)

ኤሌክትሮኒክ መልዕክት (ኢ-ሜይል): enadet1972@gmail.com

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር (ኢመየብማ) ለትርፍ ያልተቋቋመ እና በመስማት የተሳናቸው እና በጥቂት የሚሰሙት ጓደኞቻቸው አማካይነት የተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ማኅበር ነው። ማኅበሩ በ1963 ዓ.ም ተቋቁሞ በ1964 የመንግስት የፀጥታ ጥበቃ መሥሪያ ቤት ይባል በነበረው በይፋ የተመዘገበ ሲሆን፣ በአዲሱ የበጎ አድራጎት እና ማኅበራት አዋጅ በፌዴራል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማኅበራት ኤጀንሲ እንደ አዲስ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበሮች ድንጋጌዎች መሠረት በ2003 እንደገና እንዲመዘገብ የተደረገ፣ በ2012 ዓ.ም. ደግሞ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት ተመዝግቧል።

ማኅበሩ በተመረጡ የማህበሩ አባላት በሙሉ የሚመራ እና የሚተዳደር ማኅበር ነው።

ማኅበሩ በአሁኑ ጊዜ 28 ቅርንጫፎች አሉት። አገልግሎቱንም በአገሪቱ ውስጥ ላሉት መስማት የተሳናቸው ሁሉ ለማዳረስ እየሞከረ ነው። በአገሪቱ ያለው የበይነመረብ ግንኙነት በጣም እየተሻሻለ ነው። ስለሆነም መስማት ለተሳናቸው በጣም ሩቅ ቦታዎች ያሉትም እንኳን ቢሆኑ ማኅበሩ ከአባላቱ እና ከሌላው ዓለም ጋር ለመገናኘት እንዲችል ይህንን ድረ-ገፅ አበልፅጓል።

ማኅበሩ የዓለም መስማት የተሳናቸው ፌደሬሽን ኣባል ነው

WFD Logo

ኢመየብማ የዓለም መስማት የተሳናቸው ፌደሬሽን አባል (ዓመየፌ) አባል ነው። ከ1965 ጀምሮ አባል ሆኗል። እ.ኤ.አ. በ1975 አሜሪካ ውስጥ በዩናይት ስቴትስ በተደረገው የመስማት የተሳናቸው ፌደሬሽን አጠቃካይ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካፈለ። እ.ኤ.አ. በ2015 በኢስታንቡል፣ ቱርክ በተካሄደው አጠቃላይ ጉባኤም ተካፍሏል። በሁለቱም መካከል በተካሄዱት ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ውስጥ በአምስት የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች የተሳተፈ ሲሆን፣ እ.ኤ.ኣ እስከ 2015 ረደስ በአጠቃላይ በሰባት የፌደሬሽኑ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ውስት የማኅበሩ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ኢመየብማ የአካል ጉዳተኞች ማህበራትን አቅፎ የሚገኘው የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢአጉብማፌ) መሥራቾች ከሆኑት አባላት መካከል አንዱ ነው።

ተግባራት

በኢመየብማ የሚሠሩ ተግባራት በመስማት ለተሳናቸው ህጻናት፣ በመስማት ለተሳናቸው ወጣቶች እና በላይ መስማት የተሳናቸው ሴቶች አትኩሮት ያደረጉ ናቸው። ዋና ዋናዎቹ ጭብጦች መስማት የተሳናቸው የሚመለከቱ ሆነው ህጻናት ትምህርት፣ የወጣቶች የሥራ ስምሪት፣ የምልክት ቋንቋ እድገት፣ የመዝናኛ ተግባራት (የስፖርት)፣ የየህክምና አገልግሎት፣ የምልክት ቋንቋ የማስተርጎም አገልግሎት፣ የመስማት ለተሳናቸው ባህል፣ በኤች.አይ.ሺ/ኤይድስ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ናቸው። ተግባሩን በመንግሥታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ይተገብራል።

ማኅበሩን የመሠረቱት መስማት የተሳናቸው ሰዎች በአብዛኛው ወጣት ነበሩ። አሁን ማኅበሩ ከተመሠረተ ከ45 ዓመታት በኋላ እነዚህ አባላት አረጋውያን (አዛውንቶች) ሆነዋል። ኢ.ኤ.አ. ከታኅሣሥ 2015 ጀምሮ መስማት የተሳናቸው አረጋውያን የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ክለብ ያቋቋሙ ሲሆን፣ ማኅበሩም የመስማት የተሳናቸው አረጋውያን ዘርፍ ሊኖረው ችሏል። በዕድሜ የገፉ አባሎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር ማኅበሩ ከዚህ በፊት አጋጥመውት የማያውቁ አዳዲስ ከዕድሜ መግፋት የተያያዙ ችግሮች ሊያጋጥሙት ይችላሉ። ስለዚህ ከአሁኑ ጀምሮ ስለ መስማት የተሳናቸው አረጋውያንና ስለ ፍላጎቶቻቸው ማሰብና ማቀድ ቢጀምር መልካም ይሆናል።