የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ሐምሌ 15 ቀን 1994 ዓ.ም. የትምህርት ዓመት መጨረሻ ወቅት

የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ሐምሌ 15 ቀን 1994 ዓ.ም.
የትምህርት ዓመት መጨረሻ ወቅት
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

የኢመየብማ ኮአከአሽን መዋዕለ ሕፃናት ዓለም አቀፍ የሕፃናት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ከተከበረ በኋላ የተቋቋመ ነው። በወቅቱ በማዘር ቴሬዛ የሚካሄድ የበጎ አድራጎት እህቶች የሚባል ማኅበሩ ካለበት አካባቢ አቅራቢያ ይገኝ ነበር። ከነዚያ እህቶች መካከል ሁለቱ በድርጅታቸው እንክብካቤ ሥር የነበሩ ሁለት መስማት የተሳናቸው ሕፃናት (አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት) ይዘው በመምጣት ማኅበሩ እንዲያስተምርላቸው ጠየቁ። ማኅበሩም ጥያቄያቸውን ላለመቀበል እና አላስተምርም ለማለት የማይቻለው ሆኖ አገኘው። በመሆኑም ሕፃናቱን በሳምንቱ የሥራ ቀናት ውስጥ በየቀኑ ለግማሽ ቀን ለማስተማር ተስማማ። ይህ የሆነው በ1974 ዓ.ም. ነበር።

የተጨማሪ ሕፃናት መምጣት

የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች በ1974 ዓ.ም.

የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች በ1974 ዓ.ም.
(ፎቶ: ከማኅበሩ ስብስብ፤
ይህ ፎቶ ከዩኔስኮ በመጡ ባለሙያዎች የተነሳ ነው።
ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት)

ሌሎች ወላጆችና የማኅበሩ ወዳጆች ማኅበሩ ሕፃናት ማስተማር መጀመሩን እንዳዩ ሌሎች ሕፃናትም ማምጣት ጀመሩ። በዚህ መንገድ የማኅበሩ መዋዕለ ሕፃናት ሊጀመር ቻለ። ይህ በሆነበት ወቅት ዓለም አቀፍ የሕፃናት አሰርተ ዓመታት በተባበሩት መንግሥታት ታውጆ እየታሰበ ነበር። ማኅበሩም ይህንን አስታኮ ለመስማት የተሳናቸው የሚሆን የሕፃናት መዋያ ለማቋቋም የሚያስችል የፕሮጄክት ሃሳብ አዘጋጅቶ ለዩኔስኮ የጋራ ተግባር ፕሮግራም ላከ። የማኅበሩ የፕሮጄክት ሃሳብ ተቀባይነት በማግኘቱም በዩኔስኮ የተመረጡ ፕሮጄክቶች በዩኔስኮ ወዳጆች ማኅበራትና ክለቦች ታውቀው እንዲደገፉ ለማድረግ በሚታተሙበት መጽሔት (ብሮሸር) ውስጥ ለመታተም በቃ።

የተመረጡት ፐሮጄክቶች ብሮሸሩ ውስጥ ታትመው ከተሰራጩ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ማኅበሩ እርዳታዎች ይደርሱት ጀመር። እርዳታው ይመጣ የነበረው "ዩኑም ቼክ" ተብሎ ይታወቅ በነበረው ነበር።

ዩኑም ቼክ ዋና ዓላማው ጥቃቅን ግዢዎች ለማካሄድ እንዲቻል ተብሎ የተዘጋጀ ነበር። ኢመየብማ የፈለገው ግን ለሕፃናት መዋያው በቋሚነት የሚያገለግል ቤት ለማሠራት ነበር። በዚያን ወቅት ለማኅበሩ የሚሆን ቦታ ለማግኘት ከመንግሥት ተስፋ ተሰጥቶት ነበር። ነገር ግን በደርግ ጊዜ በነበረው ያልተረጋጋ ሁኔታ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ለማኅበሩ ቦታ እንዲሰጥ ተወስኖ የነበረውን ውሳኔ እንዲፈጸም ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። በመጨረሻ ከመንግሥት ለውጥ በኋላ በዩኔስኮ በኩል የተሰበሰበው ገንዘብ ለማኅበሩ የሕፃናት መዋያው አገልግሎት የሚሆን ቤት እንዲገዛበት ተወስኖ ቤት ለመግዛት ተቻለ።

የገንዘብ እርዳታ ምንጭ

የኢመየብማ ሕፃናት መዋያ የትምህርት ዓመት መጨረሻ ሐምሌ 13 ቀን 1994 ዓ.ም.

የኢመየብማ ሕፃናት መዋያ የትምህርት ዓመት መጨረሻ
ሐምሌ 13 ቀን 1994 ዓ.ም.
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

በዩኔስኮ በኩል ከዩኔስኮ ወዳጆች ለማኅበሩ ከተሰበሰበው ውስጥ አባዛኛው የተገኘው ከኔዘርላንድስ የዩኔስኮ ማዕከል ነበር። ቀሪው ደግሞ የተገኘው ከጃፓን የዩኔስኮ ማኅበራት ፌደሬሽን ነበር። በፌደሬሽኑ አስተባባሪነት ብዙ ጃፓናውያን ዩኑም ቼክ እየገዙ ለማኅበሩ በፖስታ ቤት በኩል ልከዋል። ከጃፓናውያኑ ሌላ ከአሜሪካ ሁለት ተማሪዎች፣ ከእንግሊዝ ደግሞ አንድ ግለሰብ ዩኑም ቼክ ገዝተው ለማኅበሩ ልከዋል።

ከላይ የሚታየው በዩኔስኮ ፎቶግራፈር የተነሳውን ፎቶ ቀረብ ብሎ በጥልቀት ለተመለከተው ሰው (ፎቶውን በትልቁ ለማየት ይጫኑት) ሕፃናቱ የተቀመጡት በፍራፍሬ ሳጥን ላይ መሆናቸውን፣ ጠረጴዛው ደግሞ ዕቃዎችን በመርከብ ለመላክ ከሚያገለግሉ ቁርጭራጭ እንጨቶች የተገጣጠመ መሆኑን ያስተውላል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ይህ ችግር ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ድርጅት (ዩኒሴፍ) በተገኘ አነስተኛ ግን በጣም ጠቃሚ የነበረ እርዳታ ጠረጴዛዎችና የሕፃናት ወንበሮች በማሠራት መፍትሔ ሊገኝለት ተቸሏል። የመጫወቻና ሌሎች የመማርያ ዕቃዎች ደግሞ ከቀድሞው ምሥራቅ ጀርመን መስማት የተሳናቸው እና በከፊል መስማት የተሳነናቸው ፌደሬሽን በእርዳታ ተገኝተዋል።

ቤት ተገዛ

የመዋያው ሕፃናት ሰኔ 11 ቀን 2003 ዓ.ም.

የመዋያው ሕፃናት ሰኔ 11 ቀን 2003 ዓ.ም.
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

በእርዳታ የተገኘው ገንዘብ ማኅበሩ ለሕፃናት መዋያው ብቻ እንዲያገለግል የታለመ ቤት ለመግዛት ያስቻለው ሲሆን መዋያውም ወደ ቤቱ በ1990 ዓ.ም. ለመግባት ችሏል። እስከዚያው ድረስ የሕፃናት መዋያ አገልግሎቱ ከማኅበሩ ጽሕፈት ቤት በአንድ ጠባብ ክፍክ ውስጥ ሲሰጥ ቆይቶ በዛኒጋባ መልክ ተገንብቶ ወደ ነበረው እና ዝናብ፣ የፀሐይ ሙቀት እና ንፋስ መከለል ወደማይችለው አዳራሽ ተዛውሮ ቆይቶ ነበር።

ቢሆንም አሁን የሕፃናት መዋያው ያለበት ቤትም ቢሆን ብዙ ጉድለቶች አሉበት። ቤቱ በመጀመሪያ ሲገነባ ለመኖርያነት የተገነባ ሲሆን ዲዛይኑም ለመኖርያ ቤትነትም ቢሆን መጥፎ ነው። በመሆኑም ክፍሎቹ ለማስተማሪያነት ብቁ አይደሉም። የቤቱ አንዱ ጥሩው ነጥብ የሚገኝበት አካባቢ ከከተማው መሃል አቅራቢያ እና ተመራጭ በሆነ ቦታ መገኘቱ ነው።

የበጎ አድራጊዎች ጥረት መና ሆኖ አልቀረም

ከመጀመሪያዎች የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ጥቂቶቹ ታኅሣሥ 21 ቀን 2004 ዓ.ም.

ከመጀመሪያዎች የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች ጥቂቶቹ
ታኅሣሥ 21 ቀን 2004 ዓ.ም.
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

የእርዳታ ሰጪዎች ጥረት መና አለመቅረቱና ውጤት መስጠቱ ማየጥ እጅግ ደስ ያሰኛል። ብዙ መስማት የተሳናቸው ሕፃናት በሕፃናት መዋያው የመጠቀም ዕድል አግኝተዋል። እንዳንዶቹ በአሁኑ ጊዜ የራሳቸው ቤተሰብ አፍርተዋል፤ የአባትነት፣ የእናትነት እና ሌላም ኃላፊነት መሸከም የሚችሉ ብቁ ዜጎች ሆነዋል።

የመዋዕለ ሕፃናቱ ስም

የዩኔስኮ የጋራ ተግባር ፕሮግራም ላደረገው አስተዋጽኦ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የኢመየብማ ሕፃናት ኢመየብማ ኮአክሽን መዋዕለ ሕፃናት ተብሎ እንዲታወቅ ማኅበሩ ወስኗል።

የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ሰቤ 11 ቀን 2003 ዓ.ም.
(ፎቶ: ተክለሃይማኖት ደርሶ)

የኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ፕሮጄክትን የረዱ ግለሰቦችና ድርጅቶች

ከዚህ ቀጥሎ በሚታየው ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱት ግለሰቦችና ድርጅቶች ለኢመየብማ መዋዕለ ሕፃናት ፕሮጄክት እርዳታ ያደረጉ ናቸው። ማኅበሩ መውዕለ ሕፃናቱ የሚገኝበትን ቤት ለመግዛት የቻለው እነሱ ባደረጉት እርዳታ በተገኘ ገንዘብ ነው።

ለኢመየብማ ኮአክሽን መዋዕለ ሕፃናት መቋቋም የረዱ አጋሮች

የዕርዳታ ሰጪ ስም አገር ዕርዳታ የተደረጉባቸው ዓመቶች የዕርዳታ ብዛት
A friend of NYO U.S.A. 1981 1
Aizu UNESCO Association Youth Club Japan 1983 1
Ms. Akiko Yamazaki Japan 1982, 1983 4
Mr. Akira Satomura Japan 1982 1
Anna Gilmore U.S.A 1980 1
Anonymity Japan 1982, 1983 4
Mr. Atsushi Tani Japan 1981 1
Ms. Chiaki Kato Japan 1984 1
Mr. Eiji Ogino Japan 1981 1
Ms. Eiko Matawari Japan 1981 1
Ms. Eiko Mizuno Japan 1983 1
Dr. F. H. Tunnissen
UNESCO CENTRUM NEDERLAND
The Netherlands 1979, 1980, 1981, 1982, 1983, 1984, 1985 9
Fuji Junior High School Japan 1981 1
Ms. Fukiko Yamada Japan 1982, 1983, 1984, 1987, 1988 6
Ms. Fumie Nagabuchi Japan 1981 1
Gyosei-Gakuen Kindergarten Japan 1982 1
Hakodate Club of the Japan Region Japan 1982 1
Hikari UNESCO Youth Club Japan 1982 1
Mr. Hirofumi Mitake/Miyake? Japan 1983 1
Hirosaki Club of the Jaoan Region, Japan 1981 1
Mr. Hisao Otsuki Japan 1981 1
Hirokawa High School UNESCO Club Japan 1982 1
International Year of the Child Memorial Hall Japan 1983 1
Ishikawa-ken UNESCO Association Japan 1982 1
Iwanoda Junior High School, Class No. 1 of the 3rd Grade Japan 1982 1
Mr. J. Roelands The Netherlands 1979 1
Mr. J. Jackson England 1980 1
Karatsu Club of the Japan Region Japan 1982 1
Kawaguchiko UNESCO Association Japan 1988 1
Kawasaki/Kwasaki(?) Club of the Japan Region Japan 1981, 1982, 1983 3
Ms. Kazuko Kitani Japan 1981, 1982 2
Ms. Keiko Takeda Japan 1987, 1988 2
Ms. Keiko Tsuda Japan 1988 1
Kindergarten of Gyosei Gakuen Japan 1988 1
Kinjo-Gakuin University UNESCO Club Japan 1985 1
Kisarazu UNESCO Association Municipal Board of Education Japan 1982 1
Mr. Kiyoshi Tokiwa Japan 1983, 1988 4
Kiyuna St. Andre School Japan 1987 1
Kokusai-Rikai-Bu Morikoka-Kita High School Japan 1982 1
Kokusai-shinzen Club, Dokkyo University Japan 1982 1
Kushiro Club of the Japan Region Japan 1982 1
Ms. Maie Konno Japan 1981 1
Mr. Masao Suzuki Japan 1981 1
Michael & Cyrus Lincoln U.S.A. 1981 1
Ms. Mieko Tanabe Japan 1981 1
Mr. Minoru Murata Japan 1981 1
Nabari UNESCO Association Japan 1988 1
National Federation of UNESCO Associations in Japan Japan 1981, 1982, 1988 3
Nobeoka Club of the Japan Region Japan 1982 1
Ms. Noriko Miyaka Japan 1985 1
Ms. Noriko Miyazaki Japan 1984 1
Okinawa UNESCO Association Japan 1988 1
Okinawa-Ken UNESCO Association Japan 1987 1
Oota UNESCO Association Japan 1982 1
Ota Art Association Japan 1981 1
School of Mission Board in Furuichi Japan 1982 1
Senoue Primary School Japan 1984 1
Shinobu Kato Japan 1982 1
Shiroishi UNESCO Association Japan 1985 1
Suginami UNESCO Association Japan 1982, 1987 2
Takasaki UNESCO Association Japan 1981 1
Ms. Tetsu Kimura Japan 1981 1
Tomioka UNESCO Association Japan 1984 1
Tomioka UNESCO Youth Club Japan 1984 1
Tottori UNESCO Association Japan 1988 1
Tsurugaya Junior High School Japan 1987 1
Mr. Tsuyoshi Obagawa Japan 1983, 1985 2
Ms. Yoshie Mine Japan 1985 1
Mr. Yoshio Saito Japan 1985 1
Mr. Yoshiyuki Hakamada Japan 1981, 1983 2
Mr. Yukio Imaoka Japan 1981 1
Ms. Yumi Tominaga Japan 1985 1