የኢመየብማ የሴቶች ዘርፍ
ማኅበራችን ውስጥ ከረጂም ጊዜ ጀምሮ የሴቶች ዘርፍ በህልውና ቆይቷል። ከ1960ዎቹ ጀምሮ "ሄለን የስፖርት ቡድን" የሚባል መስማት የተሳናቸው ሴቶች አባሎቻችንን በስፖርት እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ የሚያደርግ ቡድን ነበረን። ቡድኑ ከጊዜ በኋላ ወደ የሴቶች ዘርፍ ሊያድግ ችሏል።
መስማት የተሳናቸው ሴቶች አባሎች በማኅበራችን አመራር ከጅምሩ ሲሳተፉ ቆይተዋል። ከነዚህ ሴቶች መካከል በቀደምትነት የሚጠቀሱት ከሕግ አንጫር የማኅበሩ መሥራቾች ተብሎ የሚቆጠሩት የመጀመሪያው የማኅበራችን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባሎች መካከል አንዲት ሴት አባላc ይገኙ ነበር። አሳቸውም ወ/ት ስመኝ ወልደብርሃን ናቸው። የሳቸውን አርአያነት ተከትለው ሌሎች ሴት አባሎች በማኅበሩ አመራርነት ሲሳተፉና አሁንም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ወረርcኝ መከሰት ሴቶች አባሎቻችን ተጨማሪ ሚናዎች እንዲኖሩዋቸው አድርጓል። ሴቶች አባኖቸቸ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በመዋጋት በሰልጣኝነት፣ በአሰልጣኝነት፣ና በመሪነት ቦታዎች በመሳተፍ ቀዳሚ ስፍራ እንዲኖራቸው ሆነዋል። በማኅበራችን ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ዝግጅት ሲደረግ ያለ ሴቶች አባሎቻችን ተሳትፎ ስኬት ያገኛል ተብሎ በፍጹም የማይታሰብ ነው።
የኢመየብማ ሴቶች አባሎች በክልሎች የሚገኙ መስማት የተሳኛቸው እህቶቻቸውንን ወንድሞቻቸውን ለማንቃት ሀሩርና ቁር፣ ዝናብና ንፋስ ችለው ከአዲስ አበባ በመነሳት እስከ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ጂግጂጋ፣ ዓዲግራት፣ ጎንደር፣ አሳኢታ፣ እና ሌሎች ቦታዎችም ድረስ ሄደዋለል። ድካማቸው ከንቱ ሆኖ አልቀረም። በአሁኑ ጊዜ ብዙ በክልሎች የሚገኙ መስማት የተሳናቸው በማኅበሩ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። እነዚህ እንቅስቃሴዎቻቸው በዋናነት ከፊንላድ መስማት የተሳናቸው ማኅበር፣ እንዲሁም በየክልሎቹ ባሉ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮዎችና ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኘ ድጋፍ የተከናወኑ ናቸው።