አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ፡- በአቻ ለአቻ ትምህርት መስማት የተሳናቸው ሴቶችን ማብቃት፣ ሁለተኛ ዙር
ሰኔ 25 ቀን 2014 - የኢመየብማ ባልደረባ
አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ የተሰኘው በአውስትራሊያ ኤምባሲ የሚደገፈው ፕሮጄክት ሁለተኛ ዙር 46 ሴቶችን ወንዶች የአቻ ለአቻ አሠልጣኞች ሥልጠና ተካሄደ።
በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ 24 የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር ቅርንጫፎች የተወከሉ 46 የመስማት የተሳናቸ ሴቶችና ወጣቶች ተወካዮች በአዳማ ራስ ሆቴል የሁለት ቀናት ሥልጠና ወሰዱ። የሁለት ቀኑ ሥልጠናው በአውስትራሊያ ኢምባሲ የሚደገፈው አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ ፕሮጄክት አካል ሲሆን ዓላማው ጾታዊ ጥቃትን ሴቶችና ወንዶች በጋራ መከላከል በሚችሉበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነበር። በተጨማሪም ሠልጣኞቹ በአድቮከሲ ስልቶች ላይ ሰፋ ያለ ሥልጠና ወስደዋል። ተወካዮቹ ከሥልጠናው ባገኙት ክህሎት በጾታ ጥቃት ላይ በጋራ ከመሥራት በተጨማሪ በጋራ መብቶቻቸው ላይ እንዴት መሥራት እንደሚችሉ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
ከሥልጠናው ጎን ለጎንም እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በመቀጠልና መስማት የተሳናቸው ሴቶችንና ወጣቶችን ማብቃትና በማኅበሩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ በሚችሉበት መንገድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ መጨረሻም ለአሠራር እንዲመች ብሔራዊ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፍ ኮሚቴዎች ተመስርተዋል። ብሄራዊ የሴቶችና የወጣቶች ዘርፎች ማቋቋምና አመራሮችን መሰየም ማኅበሩ ለበጀት አመቱ ከያዛቸው እቅዶች መካከል ነበሩ። የብሔራዊ ማኅበሩ አመራር መስማት የተሳናቸው አስፈላጊውን ማመቻቸት ለማድረግ የጀመረውን ጥረት አጠነክሮ ለመቀጠል ቁርጠኝነቱን ረጋግጧል።