መግለጫ፡- ኢመየብማ የተቋቋመበት 50ኛው ዓመት ይከበራል።
ነሐሴ 12 ቀን 2014 - የኢመየብማ ባልደረባ
አስደሳች ዜና!
የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሄራዊ ማኅበር ከተመሰረተ 50 አመት ያለፈው መሆኑ ይታወቃል፡፡
በኮቪድ-19 ምክንያት በተጣሉ ክልክላዎችና በሀገር ውስጥ አለመረጋጋት ምክንያት ማኅበሩ የ50ኛ ዓመት
ክብረበአል ማክበሩን በተደጋጋሚ ለማሰተላላፍ ተገዶ ነበር፡፡ አሁን ሁኔዎች ከበፊቱ የተሻሉ ስለሆኑ
በዓሉን ከመጪው የዓለም አቀፍ መስማት ተሳናቸው ማኅበረሰቦች
ሳምንት ጋር
“ሁሉን አካታች የሆኑ ማኅበረሰቦች በመገንባት የ50 ዓመት ድሎቻችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን”
በሚል መሪ ቃል ሥር በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶችን አጠናቋል፡፡
መቼ? ከጥቅምት 1- 6, 2015 ዓ.ም.
በዓሉ ምን ያካትታል?
ለሳምንት የሚቆየው በአል የሚከተሉትን የተለያዩ ፕሮግራሞች ያካትታል፤
-
ለሁለት ቀናት የሚቆይ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ታላቅ ኤክስፖ / ኢግዚቢሽን
-
የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ
-
የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፖች
-
የፓናል ውይይት
-
የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የበአሉ የአዳራሽ አከካባር
-
ተቋርጦ የነበረው የብርታት መጽሄት ልዩ እትም
እንዴት መሳተፍ ይችላሉ?
-
ለመጽሄት የተለያዩ መጣጥፎችን በመላክ፤ አስተማሪ የሆኑ እውነተኛ ታሪኮች፣ ወጎች፣ መጣጥፎች፣ ማስታወሻዎች፣ ግጥሞች፣ ትዝታዎች፣ ትዝብቶች፣ ዜናዎች:: ጽሁፎች መላክ የሚቻለው በሶፍት ኮፒ ብቻ ሲሆን በኢሜይል፣ በቴሌግራም መላክ ወይም በማኅበሩ ቢሮ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይቻላል:: ጽሁፍ ለማስገባት የመጨረሻ ቀን ነሐሴ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ነው፡፡
-
በኤክስፖ / ታላቅ ኢግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ፤
ምን ሊያቀርቡ ይችላሉ?-
የተለያዩ የእደ ጥበብ ሥራዎች፤ የእንጨት፣ የብረት፣ የወረቀት ወዘተ. ሥራዎች፣
-
የሥነ-ጥብብ ሥራዎች ማለትም የሥዕል ሥራዎች፣ ቅርጻቅርጽ፣
-
የኪነ-ጥበብ ሥራዎች፡- የኢምቋ ዘፈኖች፣ ዘመናዊና ባህላዊ ውዝዋዜዎች፣ ግጥሞች ቀልዶች ወዘተ፡፡
-
የግል ንግድና ሥራዎችን ለማስተዋወቅም ይፈቀዳል፡፡
-
ማንኛው ምንም አይነት የመስማት የተሳናቸውን ችሎታ ሊያሳዩ የሚችሉ ሥራዎችና ዝግጅቶች ሁሉ በኢግዚቢሽኑ ላይ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ በኢግዚቢሽኑ ላይ ለመሳተፍ በቅድሚያ የፍላጎት ማሳያ ፎርም ሞልቶ ማስገባትና ፍቃድ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ፎርሙን በኤምይል መጠየቅ ወይም በአካል ቢሮ በመምጣት መውሰድ ይቻላል ለተጨማሪ መረጃዎች የፌስቡክ ገጻችንን ወይም የዌብሳይታችንን ይከታታሉ ወይም በሚከተለው ኤሜይል አድራሻ ይጠይቁን፡፡ አስተያየት ካለዎትም ላኩልን፡፡
ኤሌክትሮኒክ መልዕክት: enadpersonnel@gmail.com
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Ethiopian-National-of-the-Deaf-184843215409587/
ድረገጽ፡ www.enadet.org