ዘገባ እና አስተያየቶች


ብርታት መጽሔት ወጥቷል።

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር የተመሠረተበት 50ኛ ዓመቱን ከጥቅምት 22 - 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ባከበረበት ጊዜ “ብርታት” ተብሎ የሚታወቀውን መጽሔቱን አሳትሞ አውጥቷል። እዚህ ደግሞ መጽሔቱን በ “ሶፍት ኮፒ” ማግኘት ይቻላል።

መግለጫ ሁለት፡- ኢመየብማ የተቋቋመበት 50ኛው ዓመት ይከበራል።

ከጥቅምት 1 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ይከበራል ተብሎ የነበረው የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር ምሥረታ 50ኛ ዓመት መታሰብያ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጥቅምት 22 - 27 ቀን 2015 ዓ.ም መተላለፉ ታወቀ።

መግለጫ፡- ኢመየብማ የተቋቋመበት 50ኛው ዓመት ይከበራል።

የመጀመርያ መግለጫ
የኢመየብማ 50ኛ ዓመት ክብረበዓል ይከበራል።
(ቪዲዮ: ከኢመየብማ)

አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ፡- በአቻ ለአቻ ትምህርት መስማት የተሳናቸው ሴቶችን ማብቃት፣ ሁለተኛ ዙር

አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ የተሰኘው በአውስትራሊያ ኤምባሲ የሚደገፈው ፕሮጄክት ሁለተኛ ዙር 46 ሴቶችን ወንዶች የአቻ ለአቻ አሠልጣኞች ሥልጠና ተካሄደ።

ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በመስማት የተሳናቸው ላይ የግዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

ለአንዳንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በመስማት የተሳናቸው ሰዎች ላይ ያቶኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ተሰጠ።

የክፍት ሥራ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር በዋና ጽሕፈት ቤቱ ውስጥ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ክፍት የሥራ ቦታዎች ስላሉት ማመልከቻዎች እየተቀበለ ይገኛል። ማመልከቻ የማቅረቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአስር የሥራ ቀናት በኋላ ይዘጋል።

አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ፡- በአቻ ለአቻ ትምህርት መስማት የተሳናቸው ሴቶችን ማብቃት

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናች ብሔራዊ ማኅበር በሴቶች አቅም ግንባታ ላይ ያተኮር “አካሌ፣ መብቶቼና የመስማት ስነቴ” ፕሮጄክት ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የአውስትራሊያ ኢምባሲ ተወካዮች በተገኙበት ይፋ አደረገ፡፡

ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት 2014

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሄራዊ ማኅበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ63ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ29ኛ ጊዜ የተከበረውን የዓለም መስማት የተሳናቸው ሕዝብ ሳምንትን በደማቅ ሁኔታ አከበረ፡፡ åበዓሉ ዓርብ መስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም. መስማት የተሳናቸውና
ከተለያዩ አጋር ተቋማት የተጋበዙ እንግዶች በተገኙበት በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

ዶ/ር ሊዛ ኮፒነን ኢመየብማን ኅዳር 2008 ዓ.ም. ጎበኙ።

የ133 አገራት መስማት የተሳናቸው ማኅበራት የሚያገናኘው የዓለም መስማት የተሳናቸው ፈደሬሽን (ዓመየፈ) የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሊዛ ኪፒነን ኅዳር 2008 ዓ.ም. ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በኢመየብማ ጽሕፈት ቤት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። ወ/ት ሰሲሊያ ሃኒኮስኪ ከፊንላንድ መስማት የተሳናቸው ማኅበር የወጣቶች ዘርፍ እና በአሰልጣኝነት ምክንያት ኢመየብማን አዘውትረው የሚጎበኙት የዛምቢያዋ ወ/ሮ ዩፍሬሲያ ምበዌ አብረዋቸው መጥተዋል።

ሚስተር ኮሊን አለን የዓለም መስማት የተሳናቸው ፈደሬሽን ኢመየብማን ጎበኙ።

የዓለም መስማት የተሳናቸው ፈደሬሽን (ዓመየፈ) ፕሬዚዳንት ሚስቴር ኮሊን አለን የካቲት 18 ቀን 2007 ዓ.ም ኢመየብማን ጎብኝተዋል። ዶ/ር ሊዛ ኮፒነን የፈዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳን እና ዋና ፀሐፊ በነበሩባቸው ጊዜያት ማኅበራችንን ጎብኝተው የነበሩ ቢሆኑም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳን ማኅበራችንን ሲገበኝ ግን የሚስተር አለን ጉብኝት የመጀመሪያው ነው።

አቶ በላይ ተክሉ የዓለም መ.የ. ሳምንት 1992 ሲከበር ኢመየብማን ረዱ።

የ1992 ዓለም አቀፍ የመስማት የተሳናቸው ሳምንት ነፍሰሄር አቶ በላይ ተክሉ ባደረጉት ዕርዳታ በደመቀ ሁኔታ ተክብሮ ውሏል። አቶ በላይ ተክሉ ብዙ የሥራ እንቅስቃሴ በሚታይበት መርካቶ በተለይም ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አካባቢ በኬኮችና ጣፋጭ ምግቦች ንግድ በጣም የታወቁ ነበሩ።

ለመስማት የተሳናቸው በኤችአይቪ ኤድስ ላይ የመጀመርያው ሥልጠና በ1990 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር በ1990 ዓ.ም. ከጋሎዴት ዩኒቨርሲቲ በተገኘ ዕርዳታ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ትምህርታዊ ሥልጠና ለአባሎቹ አዘጋጅቷል።

የማኅበሩ ዜና ዘገባ ዛሬ ተጀመረ

ይህ የኢመየብማ ዜና ዘገባ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። ይህ ለአባሎችና ለሕብረተሰቡ ተጨማሪ ወቅታዊ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።